የታላቁ የኢትጵዮያ ህዳሴ ግድብ ችቦ በሐረሪ ክልል ውስጥ በሚኖረው ቆይታ ለግድቡ ለምናደርገው ድጋፍ መነቃቃት እየፈጠረ ይገኛል ተባለ፡፡

0
273

የታላቁ የኢትጵዮያ ህዳሴ ግድብ ችቦ በሐረሪ ክልል ውስጥ በሚኖረው ቆይታ ለግድቡ ለምናደርገው ድጋፍ መነቃቃት እየፈጠረ ይገኛል ተባለ፡፡

ይህም የተባለው ችቦው በክልላችን ሴክተር መስሪያ ቤቶች የሚደረገው ቆይታ በክልሉ የመንግስት ግዢና ንብረት አስወጋጅ ጽ/ቤት በተጀመረበት ወቅት ነው፡፡

4.13.09

የታላቁ ኢትጰዮጵያ ህዳሴ ግድብ ችቦ ባለፉት ሁለት ወራት በሐረሪ ክልል በተለያዩ ወረዳዎች እተዘዋወረ ለህብረተሰቡ መነቃቃት እየፈጠረ ይገኛል፡፡

ችቦው ወደ ሌላኛው ተረኛ ክልል ከማለፉ በፊትም በክልሉ በሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ቆይታ እንደሚያደርግ የሐረሪ ክልል የህዳሴ ግድብ ህዝብ የተሳትፎ ማስተባባሪያ ም/ቤት አስታውቋል፡፡

ችቦው የመጀመሪያ ቆይታውን  በሐረሪ ክልል የመንግስት ግዢና ንብረት አስወጋጅ ጽ/ቤት ሲሆን በወቅቱም የጽ/ቤቱ አድርጓል፡፡

በወቅቱ የጽ/ቤቱ ሀላፊ አቶ ነቢል  መሀዲ ለሰራተኞቹ ባደረጉት ንግግር ችቦው በመስሪያ ቤቱ በሚኖረው ቆይታ የሰራተኛውን ግንዛቤ በማሻሻል መነቃቃት ከመፍጠር አኳያ ከፍተኛ ድርሻ ይኖረዋል ብለዋል፡፡

የጽ/ቤቱ ሰራተኞችም ድጋፋቸውን አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አቶ ነቢል ገልጸዋል፡፡

አንዳንድ የጽ/ቤቱ ሰራተኞች በሰጡት አስተያየት ችቦው ወደ ጽ/ቤታቸው በመምጣጡ መደሰታቸውን ተናግረዋል፡፡

ግድቡ ስራው ሁለንተናዊ ፋይዳ አንጻር  ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ገልጸዋል፡፡

ችቦው በቀጣይ ቀናት በሌሎች በክልሉ በሚገኙ መስሪያ ቤቶችም እንደሚዘዋወር  ወቅት ተገልጻል፡፡

ዘጋቢ አፈንዲ መሀመድ

NO COMMENTS