የትምህርት ግብአት እጥረት በትምህርት ጥራት ላይ ተጽእኖ እየፈጠረ መሆኑን ያነጋገርናቸው ትምህርት ቤቶች ገለፁ፡፡

የትምህርት ግብአት እጥረት በትምህርት ጥራት ላይ ተጽእኖ እየፈጠረ መሆኑን ያነጋገርናቸው ትምህርት ቤቶች ገለፁ፡፡

አቶ ተወከል ረሺድ የድሬ ጠያራ 2ተኛ ደረጃ ት/ቤት ርዕሰ መምህር ናቸው ትምህርት ጥራት የሚረጋገጠው አስፈላጊው ግብአት ከተሟላ መሆኑን  - ቢሆንም በት/ቤታቸው የትምህርት ግብአት እጥረት ስላለ ስራቸው ላይ ጫና እየፈጠረባቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

 

በዚህም ላይ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራበት ይገባል ሰሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

 

የሸኪብ አብዱላሂ 2ተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አቶ ጃፈር መሐመድ በበኩላቸው እስካሁን ከአቅርቦት ጋር ተያይዞ የሚያስፈልገውን ለማሟላት ጥያቄ ያቀረበልን አካ የለም ብለዋል፡፡

 

ሱልጣን አሊዩ መሐመድ በክልሉ ትምህርት ቢሮ ባለሙያ ናቸው ተፎካካሪ እና ብቁ የሆኑ ተማሪዎች ለማፍራት አስፈላጊው የምህርት ግብአት ሊየትምህርት ማስረጃሟላ ይገባል ብለዋል፡፡

 

በዚህ ረገድ የትምህርት ቤቶች ርዕሳነ መምህራን ተገቢውን ጥያቄ በማቅረብ በኩል  ክፍተት እንዳለ አንስተዋል፡፡

 

እንደ ሀገር አቀፍና ከትምህርት ግብዘት ጋር ተይይዞ ችግር እንዳለ የገለፁት አቶ ሱልጣን የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ጽ/ቤት ለማቅረብ ግዢዎች ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራ ይገባል ብለዋል፡፡

 

የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ጽ/ቤት በበኩሉ ከ2005 ጀምሮ በተሰጠ ሁኔታ የመንግስት ንብረት ግዥ ላይ ጥሩ ስራ እየሰራ መሆኑን ነው የገለፁት፡፡

 

የሚቀርቡ ጥያቄዎችን በአፋጣኝ ምላሽ ለመስጠጥ እየሰራ መሆኑን ገልጻል፡፡  

     

ትምህርት ግብአት ሲገዛ በጀትና ፍላጎት ላይ በመመስረት ነው ያሉት በመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ጽ/ቤት የ ICT   ሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አህመዲን ሼኽ መሐመድ ተመሳሳይ ፍላጎት ለሚያቀርቡ ተቋማት አንድ ላይ ጨረታ ወጥቶ እቃ ስለሚገዛ አልፎ አልፎ እጥረት ሊያጋጥም ይችላል ብለዋል፡፡

 

በት/ቤቶችም ሆነ በተቋማት ውስጥ የንብረት አጠቃቀም ችግር ያለ መሆኑን ጠቅሰው ንብረት በአጋቡ መጠቀም ግዴታ በማወቅ ሊሰሩ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

 

ዘጋቢ አለም ገመቹ

29 7 13