የአሚር ኑር ወረዳ ወጣቶች ሊግ አባላት ባካሄዱት ውይይት የሐረሪ ብሄራዊ ጉባኤ ምርጫን በተመለከተ ምርጫ ቦርድ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውሳኔን እንዲከበር ጠይቀዋል፡፡

የአሚር ኑር ወረዳ ወጣቶች ሊግ አባላት ባካሄዱት ውይይት የሐረሪ ብሄራዊ ጉባኤ ምርጫን በተመለከተ ምርጫ ቦርድ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውሳኔን እንዲከበር ጠይቀዋል፡፡

አባላቱ በውይይቱ ወቅት እንዳነሱት የሀረሪ ጉባኤ ምርጫ ጉዳይ የሐረር ህዝብ የውክልና መብትን የሚመለከት በመሆኑ መብታችን እንዲከበር የጋራ የሆነ ጥብቅ አቋም ይሆናል ብለዋል፡፡

እንደ ሀረሪ ወጣት የህዝባችን መብት እንዲከበር ፅኑ አቋም ይዘናል ያሉት አሚር ኑር ወረዳ ወጣቶች የሀረሪ ህዝብ መብት እንዲከበርም ህጋዊ ትግላችን እና ድምፃችን ማሰማታችንን እንቀጥላለን ብለዋል፡፡

በዚህ ሀገራዊ የለውጥ ጉዞ ወቅት ምርጫ ቦርድ የያዘው አቋም ለውጡን የሚያደናቅና የሀረሪ ህዝብን ታሪክ ስልጣኔ እና አኩሪ የባህል አሻራ የማይመጥን የተሳሳተ መንገድ ነው ብለዋል፡፡

ቦርዱም በአፋጣኝ የሐረሪ ህዝብን መብት በማክበር የሀረሪ ብሄራዊ ጉባኤ ምርጫ እንዳለፉት 5 የምርጫ ግዜያት ሊካሄድ ይገባል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

12 8 13