የአባድር ልማት ማህበር ለችግርተኛ የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ አደረገ፡፡

0
208

 በዛሬው እለት ችግርተኛ የህብረተሰብ ክፍሎች የምግብና የአልባሳት ድጋፍ አደረገ፡፡

የአባድር ልማት ማህበር ከተቋቋመ አጭር ጊዜ ቢሆንም ከተለያዩ አባላትና ስፖንሰሮች ድጋፍ  በማፈላለግ በጤና፣ በትምህርት ሴቶችንና ወጣቶች ላይ በማተኮር የተለያዩ ድጋፎችን ያደርጋል፡፡

ማህበሩ በዛሬው ዕለትም የተቸገሩ/ አቅም ለሌላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የምግብ ፍጆታና የአልባሳት ድጋፍ አድርገዋል፡፡በመድረኩ ላይ  የማህበሩ ስራ አስኪያጅ አቶ ሙስጠፋ ሃሰን የማህበሩን አላማና የእስካሁኑን ስራዎቹን የሚዳስስ ሪፖርት  አቅርበዋል፡፡

 በዚህም አቅም የሌላቸውን ሰዎች የመደገፍ ተማሪዎችን የማስተማርና የተለያዩ ድጋፎች እየሰጠ መሆኑን ገልፀው  በቀጣይም ማህበሩ ይህን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አቶ ሙስጠፋ ገልፀዋል፡፡ ይህን ድጋፍም ቀጣይነት እዲኖረው ህብረተሰቡና መንግስት ከጎናቸው እንዲቆም ጠይቀዋል፡፡

የሰራተኛና ማበራዊ ዋስትና ፅ/ቤትና የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ፅ/ቤትም በዕለቱ የተለያዩ ድጋፎችን አድረገዋል ስትል የዘገበችው ባልደረባችን ሪሃና ጀማል ናት፡፡

NO COMMENTS