የአቦከር ወረዳ ነዋሪዎች የማህበረሰብ ጤና መድህን ዋስትና አባል ለማድረግ እየሰራ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የአቦከር ወረዳ ነዋሪዎች የማህበረሰብ ጤና መድህን ዋስትና አባል ለማድረግ እየሰራ መሆኑ ተገለጸ፡፡
የአቦከር ወረዳ ነዋሪዎች የማህበረሰብ ጤና መድህን ዋስትና አባል ለማድረግ እየሰራ መሆኑ ተገለጸ፡፡
የአቦከር ወረዳ ነዋሪዎች የማህበረሰብ ጤና መድህን ዋስትና አባል ለማድረግ እየሰራ መሆኑ ተገለጸ፡፡
የአቦከር ወረዳ ነዋሪዎች የማህበረሰብ ጤና መድህን ዋስትና አባል ለማድረግ እየሰራ መሆኑ ተገለጸ፡፡

ጤና ከሁሉም ነገር ይበልጣል እንደሚባለው ጤና ያለው ሰው ሁሉም ነገር አለው ፡፡

ከዚሁ በመነሳት በሀገር አቀፍ ደረጃ ህብረተሰቡን የጤና መድህን ዋስትና አባል ለማድረግ ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ የተጀመረውን ስራ አስመልክቶ የሀረሪ ብዙሀን መገናኛ ኤጀንሲ ከአቦከር ወረዳ  ከነዋሪዎች ከጤና ባለሞያዎችና ከወረዳው አስተዳዳር ጋር ቆይታ አደርጓል፡፡

ሀሳባቸው የሰጡት የማህረሰብ ጤና መድን ዋስትና አባላት እንደሚሉት አባልነቱ ፋይዳው ከፍተኛ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

እጅ አጠር የሆኑና በከፍተኛ ድህነት ውስጥ የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ድጋፍ እንዲደረግላቸውም ጠይቀዋል፡፡

ለአባልነት የሚከፈለው 520 ብር ለመክፈል እጅ አጥሮን  ነው እንጂ አባል ለመሆን  ፍላጎት አለን ያሉት በከፍተኛ ደህነት ውስጥ ያሉ ሰዎች አሁንም መክፈል የሚችሉት የማህበረሰብ ክፍል ግዜው ሳያልፍ ጤና መድን ዋስትና አባል ቢሆኑ ጠቀሜታ አለው ብለዋል፡፤


በአቦከር ጤና ጣቢያ የቤተሰብ ጤና ቡድን አስተባባሪ የሆኑት አቶ ወንደሰን ሰለሞን የጤና አገልግሎቱ ከቀድሞው እየተሻሻለ መምጣቱን ነው የገለፁት፡፡

አቶ ወንደሰን አክለው እንደተናገሩት የጤና መድህን አገልግሎትን ለማግኘት  በአባልነት ያልተመዘገቡበት እንዲመዘገቡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

አቦከር ጤና ጣቢያ ህብረተሰቡን የጤና መድን አባል እንዲሆን እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡

አቦከር ወረዳ ማህበረሰብ ጤና መድን ዋስትና አስተባባሪ ሲስተር ፍፁም ሚሊዮን በበኩላቸው የአቦከር ወረዳ  አካባቢ ማህበረሰበ ጤና መድህን ስራ ወደኋላ ያስቀረው በአብዛኛው ነዋሪ ጡረታ የወጡ እና ለመክፈል አቅም የሌላቸው መሆኑ እንደሆነ ነው የገለፁት፡፡

በጤና ባለሞያዎች በተደረገው የግንዛቤ ማስጨበጫ በአቦከር ወረዳ  የጤና መድን ዋስትና  የተመዝጋቢዎች ቁጥር 40 በመቶ ላይ እንሚገኝ ነው የገለፁት፡፡

ከ2009 አንስቶ የማህበረሰብ ጤና መድህን ዋስትና አባል  የሆኑ ነዋሪዎች  የመታወቂያ ካርድ  እንዳልተሰጣቸው እና  ይህም ደግሞ  በህብረተሰቡ ውስጥ ጥርጣሬ መፍጠሩንና አገልግሎቱ  የተሟላ እንዲሆን እየተሰራ ይገኛል ያሉት ሲስተር ፍፁም ለህክምና አገልግሎት የሚውሉ ግብዓቶችና መድሀኒት እንዲሟላ ለሚመለከታቸው አካላት በማሳወቅ ምላሽ እየተጠባበቁ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

የጤና መድህን ዋስትና አባል ለመሆን  እስከ 10 ቤተሰብ ያለው ሰው 520 ብር የሚከፍል ሲሆን 18 ዓመት የሞላው ሰው ካለ ተጨማሪ መቶ ብር እንደሚያስከፍል ተነግሯል፡፡

በሌላ በኩል የጤና መድህን ዋስትና አባል  የደረጃ ‘’ ሀ”  ነጋዴዎች  720 ብር የሚከፍሉ መሆኑም ተገልጻል  የቤተልሄም 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ  ትምህርት ቤት ገንዘብ ከፍለው የጤና መድህን ዋትና አባል መሆን ላልቻሉ  ለጥቂት ሰዋች ክፍያ  መፈፀመን ገለፀዋል፡፡

   የአከባብር ወረዳ  አሰተዳዳረ አቶ ሱልጣን ሳኒ ሕብረተሰቡ የጤና መድህን  ዋሰትና አባል በመሆን ተጠቃሚ እንዲሆን ሕብረተሰቡ  የማህበረሰብ ጤና መድህን  ዋሰትና አባል አንዲሆን ከሀይማኖት አባቶች እና ተሰሚነት ካላችው ግለሰቦች እየተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡

በወረዳው ውስጥ የሚገኙ እጅ አጠር የሖኑ የማህበረሰብ ክፍሎች የጤና መድህን ዋስትና ተጠቃሚ እንዲሆኑ በወረዳው ውስጥ ያሉ ባለሀብቶች ላደረጉላቸው ድጋፍ መስጋናቸው አቅርበዋል፡፡

በማህበረሰብ ጤና መድህን አገልግሎት በኩል የጥርስ ህክምና እና የኩላሊት እጥበትን ጨምሮ እስከ አዲስ አበባ ድረስ ሪፈር በመላክ የህክምና አገልግሎቶችን ማግኘት ይቻላል፡፡

   ዘጋባ ቱራ አያና
27 5  13