የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውሳኔን በማክበር በምርጫ የመሳተፍ መብታችንን ሊያከብር ይገባል ሲሉ የአባድር ወረዳ ነዋሪዎች ጠየቁ ፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውሳኔን በማክበር በምርጫ የመሳተፍ መብታችንን ሊያከብር ይገባል ሲሉ የአባድር ወረዳ ነዋሪዎች ጠየቁ ፡፡

የወረዳው ነዋሪዎች  እስካሁን ድረስ ምንም አይነት የምርጫ ካርድ እንዳልወሰዱ ተናግረዋል፡፡

የአባድር ወረዳ የሀረሪ ብሄራዊ  ጉባኤ ምርጫን በተመለከተ ከዚህ ቀደም በነበረው ውይይት ላይ ባለ 5 ነጥብ የአቋም መግለጫ ማውጣታቸውን ይታወሳል፡፡

 

የወረዳው ነዋሪዎች በዛሬው እለትም ከወረዳው እና የክልሉ አመራሮች ጋር  በሀረሪ ጉባኤ ምርጫ ዙርያ ተወያይተዋል፡፡

 

በጀጎል ልዩ ምርጫ ሁኔታ ዙርያ ምርጫ ቦርድ የያዘውን አቋም በማስተካከል ባለፉት ምርጫዎች የሀረሪ ብሄራዊ ጉባኤ አባላት የሚመረጡበትን ህጋዊ አሰራር እንዲተገብር በክልሉ መንግስት በኩል ከፍተኛ ጥረት እየተደረገና ውጤቶች እየታዩ መሆኑንም የመድረኩ አወያይ አቶ ካሊድ አብዲ  ተናግረዋል፡፡

 

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በ5ቱ የምርጫ ጊዜያት የነበረውን ህጋዊ አሰራር እንዲከተልም ተገቢው ሰነዶች ቀርበውለት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፅህፈት ቤትም በደብዳቤ መታዘዙን ተናግረዋል፡፡

 

የውይይቱ ተሳታፊ የነበሩ የአባድር ወረዳ ነዋሪዎች በሰጡት አስተያየት የሐረሪ ህዝብ    ቀደምት የስልጣኔ አሻራ በማኖር ከሚጠቀሱ ህዝቦች አንዱ መሆኑን አንስተው በተለያዩ ግዜያት ይደርሱት በነበረው ጫና ሳቢያ ቁጥሩ እንዲቀንስ መገደዱን ተናግረዋል፡፡

 

በሀገሪቱ ተግባራዊ የሖነው የፌደራል ስርዓትም ለሀረሪ ህዝብ ያጎናፀፈው መብትን ተከትሎ  የሐረሪ ብሄራዊ ጉባኤ የሀረሪ ህዝብ የሚወከልበት  ሆኖ ሳለ እስካሁን ድረስ ግን ለጉባኤው ምርጫ የሚሳተፉበት ልዩ የመራጭነት ካርድ አለመዘጋጀቱ እንዳሳሰባቸው ተናግረዋል፡፡

 

በቀጣዩ ምርጫ ላይ የሐረሪ ህዝብን ተሳትፎየሚገድብ አካሄድ በምርጫ ቦርድ በኩል የተያዘ በመሆኑ በአፋጣኝ መብታችንን ሊከበር ይገባል ሲሉ የአባድር ወረዳ ነዋሪዎች  ገልፀዋል፡፡

 

ዘጋቢ በሀር መሀመድ

11 8 13