የእስልማ ሀይማኖት መሪዎች ሽብርተኝነት በማውገዝ በአውሮፓ ሀገራት ጉብኝት እያካሄዱ ይገኛሉ፡፡

0
189

ከተለያዩ ሀገራት የተወጣጡ የእስልማ ሀይማኖት መሪዎች ሽብርተኝነት በማውገዝ በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት ጉብኝት እያካሄዱ ይገኛሉ፡፡
የሀይማኖት መሪች የሽብር ጥቃት በደረሰባቸው የአውሮፓ ሀገራት ከተሞች ጉብኝት እያካሄዱ ይገኛሉ፡፡
በዋናነት ሽብርተኝነትን በማውገዝ እና የሽብር ጥቃት ከሀይማኖት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌለው ለማመልከት የተዘጋጀው ይህ የሀይማት አባቶች ጉብኝት በሁለተኛው ቀናቸው በጀርመን ዋና ከተማ በርሊን ተገኝተዋል፡፡
ከፈረንሳይ ፤ከቤልጄም ፤ከእንግሊዝ የተወጣጡ እነዚህ የሀይማኖት አባቶች በስድስት ቀን ጉብኝታቸው በእስልምና ስም እየተፈጸሙ ያሉ የሽብር ጥቃቶችን ማውገዝ እና ጥቃት በደረሰባቸው የአውሮፓ ከተሞች ተገኝተው በጥቃቱ የሞቱትን ሰዎችን ለማስታወስ አቅደው እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ፡፡
የበርሊን ዳሬ ሰላም መስጅድ ኢማም መሀመድ ጠሀ ሳቢር ሽብርተኝነት የእስልምናን ስም ለማጠልሰሸት የተቀናበረ ነው ብለዋል፡፡
ይህ ጉብኝት ለማካሄድ ያስተባበሩት አካላት እና ኢማሞቹ ሀይማኖታችን ሰላማዊ መሆኑን ለማሳየት ይህ ብቻ ማካሄድ በቂ አይደለም ሌሎች በርካታ ስራዎችም ያስፈልጋሉ ብለዋል፡
ይህ ሽብርተኝነትን የሚያወግዘው የአውቶቢቭ ጉብንት የሽብር ጥቃት የደረሰባቸው ስፍራዎች ላይ ጉብኝት የሚደረግ ሲሆን በመጀመሪያ ከፓሪስ ጉዞው ሲጀመር 30 ሚሆኑ ኢማሞች የነበሩ ሲሆን አሁን ወደ 60 ሚጠጉ ኢማሞች ከተለያዩ ሀገራት የተሰበሰቡ መሆኑን ተናግሯል፡፡
ዘገባው የዩሮ ኒውስ ነው
3/11/09

NO COMMENTS