የኮሮና ቫይረስ መስፋፋት ለመከላከል የጥንቃቄ መመሪያዎችን ሕብረተሰቡ በአግባቡ መተግበር እንዳለበት ተገለፀ፡፡

የኮሮና ቫይረስ መስፋፋት ለመከላከል የጥንቃቄ መመሪያዎችን ሕብረተሰቡ በአግባቡ መተግበር እንዳለበት ተገለፀ፡፡

የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በተመለከተ የሀረሪ ክልል ጤና ቢሮና የሀረሪ ክልል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰተዋል፡፡

 

የኮሮና ቫይረስ መከላከያ መንገዶችን በተመለከተ የሀረሪ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ እና የጠቅላይ አቃቤ ሕግ ቢሮ በጋራ ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰተዋል፡፡

 

ከክልሉ ነዋሪዎች ቁጥር ጋር ሲነጻጸር በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን እና እስካሁን ከተደረገው 43ሺ በላይ የተመረመሩ ሰዎች መካከል 3351 በኮሮና ቫይረስ መያዛቨውንና ከዚህም 124 በላይ የሚሆኑት ለሕልፈተ ሕይወት መደረጋቸውን የክልሉ ጤና ቢሮ ሀላፊ አቶ ኢብሳ አብራሂም ተናገረዋል፡፡የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ በመምጣቱ በትናንታናው ዕለት ብቻ  144 ሰዎች ላይ በተደረገ ምርመራ ብቻ 51 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን አቶ ኢብሳ ኢብራሂም ተናግረዋል፡፡

 

የክልሉ ኮሮና ቫይረስ መከላከያ ማዕከል የምስራቅ ሐረርጌን ጨምሮ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ እና አንዳንድ እጥረቶች ቢያጋጥሙም የክልሉ መንግስት ከፍተኛ ትኩረት ሰቶ በመሥራቱ የተሻለ ሥራ መካሄዱ ተገልጧል፡፡

 

አገር አቀፍ ደረጃ ያጋጠመውን የኦክሲጂን እጥረት ለመቅረፍ መንግስት ተጨማሪ በጀት በመመደብ ችግሩ ደግሞ እንዲከሰት በምክትል ቢሮ ኃላፊ የሚመራ ኮሚቴ ተቋቁሞ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

 

የቫይረሱን መስፋፋት ደረጃ በተመለከተ በየሳምንቱ በሚደረግ ውይይትና ግምገማ እየተካሄደ ነው ብለዋል፡፡

 

የጤና ቢሮ ብቻውን ቫይረሱን መከላከል ስለማይችል ሕብረሰቡንና ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ተናበው በአንድነት መስራት ይገባቸዋል ብለዋል፡፡

 

በአሁኑ ወቅት የሚታየውን በመጨመር ላይ እንደሚገኝና ይህ ደግሞ ከፍተኛ ዋጋ የሚያስከፍል በመሆኑ ሕብረተሰቡ የቫይረሱን መከላከያ ዘዴዎች በአግባቡ መተግበር አለበት ብለዋል፡፡

 

የሀረሪ ክልል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ቢሮ ኃላፊ አቶ አዩብ የኮሮና ቫይረስ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል መመሪያ ወጥቶ ተግባራዊ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

 

መመሪያውን ሥራ ላይ ለማዋል ኮሚቴ ተቋቁሞ  ወደ ሥራ መግባቱን እና በመንግስታዊ ተቋማትና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ይህንን በማይተገብሩ ሰዎች ላይ ከ10 ቀን እስከ 3 አመት የሚደርስ እስራት የሚያስቀጣ መሆኑን እና ይህም በዚሁ አዋጅ መደንገጉን ነው የተናገሩት፡፡

 

ማንኛውም አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የተቀመጠውን መመሪያ መተግበር ግዴታ እንዳለባቸው ጠቁመዋል፡፡

 

በአሁኑ ሰዓት በሀረሪ ክልል በኮሮና ቫይረስ ተይዘው በጽኑ ሕማና ላይ የሚገኙ 50 ሰዎች በላይ ይገኛሉ፡፡

 

ዲኔ መሀመድ

1 8 13