የኮቪድ 19 ክትባት በዛሬው እለት በአሚር ኑር እና በአቦከር ጤና ጣቢያ ለሚሰሩ የጤና ባለሞያዎች ተሰጠ፡፡

የኮቪድ 19 ክትባት በዛሬው እለት በአሚር ኑር እና በአቦከር ጤና ጣቢያ ለሚሰሩ የጤና ባለሞያዎች ተሰጠ፡፡

  ይህ ክትባት የተዘጋጀው በሀረሪ ክልል ጤና ቢሮ ነው ተብሏል፡፡

 

ክትባቱ የወሰዱት የጤና ባለሞያዎች እንዳሉት ክትባቱን በቅድሚያ መውሰዳቸው ለእነሱ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው የተናገሩት ፡፡

 

የኮቪድ 19 ክትባት በአሚር ኑር እና በአቦከር ጤና ጣቢያ የሚሠሩ የጤና ባለሞያዎችን ጨምሮለሌሎች ወረዳዎች ጤና ባለሞያዎችም  ተሰቷል፡፡

 

ክትባቱን ሲወስዱ ያገኘናቸው ባለሞያዎችም ክትባቱን ጉዳት ያስከትላል ተብሎ የሚነዛው መሰረተ ቢስ ወሬን ህዝቡ ውሸት መሆኑን በማወቅ መከተብ እንዳለበት ነው የተናገሩት ፡፡

 

አሁን የተሰጠው ክትባት የጤና ባለሞያዎችን እስከ ሶስት ወር የሚያገለግላቸው መሆኑም ተገልፃል፡፡

 

የኮቪድ ክትባት በሀረሪ ክልል ጤና ቢሮ የሚሰጥ ሲሆን በሁሉም ጤና ተቋማት ለሚሰሩ ባለሞያዎች  እየተሰጠ እንዳለም ተገልፃል፡፡

 

በቀጣይ ቀናትም በሌላ በሽታ የተጠቁ ሰዎችና እድሜያቸው ከ65 አመት በላይ ለሆኑ ዜጎች እንደሚሰጥም ተጠቁሟል፡፡

 

ትህትና ተስፋዬ

20 7 13