የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል የተቀመጠውን መመሪያ ሁሉም የክልሉ ማህበረሰብ እንዲተገብር የሀረሪ ክልል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ቢሮ አስታወቀ፡፡

የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል የተቀመጠውን መመሪያ ሁሉም የክልሉ ማህበረሰብ እንዲተገብር የሀረሪ ክልል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ቢሮ አስታወቀ፡፡

***************

የኮቪድ 19 የጥንቃቄ መመሪያን በተመለከተ የሐረሪ ክልል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ቢሮ መግለጫ አውጥቷል፡፡

 

በአገራችን ብሎም በክልሉ የኮቪድ 19 ስርጭት ከጊዜ ወደ ግዜ ተስፋፍቶ በመምጣቱና በአሁኑ ሰዓት ላይ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ በቁጥር 30/2013 ዓ.ም በወጣው አገራዊ መመሪያ መሰረት በሁሉም የክልሉን ህብረተሰብ ተፈፃሚ ሊደረግ እንደሚገባ የሐረሪ ጠቅላይ ዐ/ህግ ቢሮ ኃላፊ አቶ አዩብ አህመድ ገልፀዋል ፡፡

 

በዚህም መሰረት መመሪያው 

  1. ማንኛውም አገልግሎት ሰጪ ተቋማትና በየትኛውም የመገበያያ ስፍራ የአፍና ያፍንጫ ጭንብል እና 2 ሜትር ርቀት ጠብቆ አገልግሎቱን ማግኘት እንዳለበት እንዲሁም በማንኛዉም የትራንስፖርት አገልግሎት ላይ ሹፌሮች እንዲሁም ተሳፋሪዎች መጠቀም እንዳለባቸዉ መመሪያው ይደነገጋል፡፡

 

  1. ማንኛውም የህብረተሰብ ከመኖሪያ ቤት ውጪ በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች የአፍና ያፍንጫ ጭንብልና ሳኒታይዘር መጠቀም እንዳለበት በመመሪያው ተቀምጧል፡፡

 

 

  1. በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ በቀብር ማስፈጸሚያ ቦታዎች ላይ በህጉ የተፈቀደ ከ50 ሰው በላይ ማስፈጸም እንደማይችል መመሪያው ያዛል፡፡

 

  1. የትምህርት ተቋማት የትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው መመሪያ መሠረት ኮቪድ 19 ለመከላከል በሚያስችሉ አሰራሮች ባደረገ መልኩ የመማር ማስተማር ስርዓቱን ማካሄድ እንደሚገባቸው ሀላፊው የገለፁ ሲሆን ከዚህ በላይ የወጡትን መመሪያዎችን የሚከታተሉና የሚያስፈጽሙ ግብርኃይሎች የተዋቀረ በመሆኑ ተግባዊ በማያደርጉ የክልሉ ነዋሪዎች እስከ 3 ዓመት እስራት የሚያስቀጣ በመሆኑ የበሽታውን ስርጭት ለመግታት በሚደረገው ርብርብ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባ የክልሉ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ቢሮ አስታውቋል፡፡