የድሬ ጠያራ ወረዳ አርሶ አደሮች የዘንድሮው አመት ማዳበሪያ እና ምርጥ ዘር አቅርቦት ላይ ያላቸው ቅሬታ ገለፁ፡፡

የድሬ ጠያራ ወረዳ አርሶ አደሮች የዘንድሮው አመት ማዳበሪያ እና ምርጥ ዘር አቅርቦት ላይ ያላቸው ቅሬታ ገለፁ፡፡

የድሬ ጠያራ ወረዳ ግብርና ጽሕፈት ቤት በበኩሉ ማዳበሪያና ምርጥ ዘር በጊዜ ወደ አርሶ አደሩ ለማቅረብ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡

 

የድሬ ጠያራ ወረዳ አርሶ አደሮች ከሐረሪ  ብዙሃን መገናኛ ኤጀንሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደተናገሩት በማዳበሪያ እና ምርጥ ዘር አቅርቦት ላይ ቅሬታ ያላቸው መሆኑን ነው የገለፁት፡፡

 

እነዚህ አርሶ አደሮች እንደሚሉት በግብርና ልማት በኩል አርሶ አደሩን ትኩረት ስለነፈጉን ለአቅርቦት ችግር መጋለጣቸውን  ተናግረዋል፡፡

 

በአሁኑ ሰዓት ከብቶቻቸው ሲታመሙ ሕክምና እንደማያገኙና ማዳበሪያ ጊዜውን ጠብቆ እንደማይቀርብላቸውና በተለይም የዘንድሮው አመት እስካሁን ምንም አይት ድጋፍ እንዳልተደረገላቸው ተናግረዋል፡፡

 

  እነሱ የሚጠበቅባቸውን ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን የገለፁት አርሶ አደሮቹ ከግብርና ባለሞያዎች የግንዛቤ ትምህርትም እንዳተሰጣቸው ጠቁመዋል፡፡

 

የድሬ ጠያራ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ረመዳን ኢድሪስ የዘንድሮውን አመት ማዳበሪያና ምርጥ ዘር አቅርቦት አስመልክተው እንዳሉት ከሚያቀርቡት ምርጥ ዘር መካከል አንደኛው በቆሎ እንደሆነ እና የማሽላ  ፈንድሻ ዘር ደግሞ አርሶአደሩ እጅ ስላለ እሱን ይጠቀማሉ ብለዋል፡፡

 

የበቆሎ በየጊዜው እየተሻሻለ ስለሚሄድ /ዲኤች 661/ የተባለው በቆሎ 61 ኩንታል እንዲያደርሳቸው በግብርና ጽ/ቤት ተፈቅዶልናል ሲሉ አቶ ረመዳን ገልጸዋል፡፡ከዛሬ ጅምሮ ማቅረብ እንደሚጀምርም ነው የተናገሩት

 

ከመዳበሪያ ጋር በተያያዘ መሠረት ማሕበርና እና ዩኒየን በክልሉ የሚንቀሳቀሱ በመሆኑ ለሀሰን ጌይ ቀበሌ መሠረታዊ ማሕበር በማቅረብ በአሁኑ ሰዓት ማዳበሪያ የተራፈ በመሆኑ የአርሶ አደሩን ቅሬታ የሚፈታ እንደሆነ ና በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ነው የገለፁት፡፡

 

የድሬ ጠያራ ወረዳ ም/አስተዳዳሪ አቶ ታጅር ሻሜ የማዳበሪያ እና ምርጥ ዘር አቅርቦት በጥሩ ሁኔታ ላያ ያለ መሆኑን በመግለጽ በክልሉ ምርጥ ዘር ያለ መሆኑን የማዳበሪያ እጥረት መኖሩን ግን አልሸሸጉም፡፡

 

የግብርና ቢሮቢያነጋግሩም በማሕበር ማቅረብ እንዳተቻለ በመናገር መንግስት ማቅረብ የሚችል ማሕበር ለማቋቋም ችግሩን መፍታት አለበትም ብለዋል፡፡

 

ይህን ችግር ለመቅረፍ በአጭር ጊዜ የበላይ አካል የሚጠይቁ እንደሆነ ገልጸው ለአሁኑ ግን እጃቸው ላይ ምንም ነገር እንደሌለለና በቀበሌዎች የሚያዳርሱት ነገር የለም ብለዋል፡፡

 

ቱራ አያና

1 8 13