የፈተና ኩረጃን የሚጠየፍ የተማረ ሰው ሀይል ለመፍጠር ተማሪዎችን በስ ዜጋና በስ ምግባር ትምህርት ማነፅ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ገለፀ፡፡

በሀረሪ ክልል የፀረ ሙስ ኮሚሽን አዘጋጅነት  በድሬደዋ ከተማ ለስነ ዜጋና ለስነ ምግባር መምህራን በሙስና እና በስነ ምግባር ዙርያ ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

የስልጠናውን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር አቶ ካሊድ ኑሬ እንደገለፁት ይህ ስልጠና ለመምህራኖች የተዘጋጀው ከሙስና እና ከብልሹ አሰራሮች የፀዳ ዜጋን ለመፍጠር የስነ ዜጋና የስነ ምግባር መምህራን ያላቸው አስተዋጾ የጎላ ስለሆነ ነው ብለዋል፡፡

ተማሪዎች ከሙስናና ከስርቆት የፀዱ እንዲሆኑ እና የፈተና ኩረጃን የሚጠየፍ የተማረ የሰው ሀይል ለመፍጠር መምህራኖች  የላቀ ድርሻ እንዳላቸው ያስገነዘቡት አቶ ካሊድ መምህራን ተማሪዎችን በስ ምግባር ለማነፅ የበኩላቸውን ድርሻ  እንዲያበረክቱ ጠይቀዋል፡፡

በመድረኩ በክብር እንግድነት የተገኙት በሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ የስርዓተ ትምህርት ዝግጅትና ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጃሚዕ መሀመድ በበኩላቸው ተማሪዎችን በስ ምግባር ለማነፅ የሚያስችሉ ክበባት በሁሉም ትምህርት ቤቶች እንደቋቋሙ በማድረግ የትምህርት ሴክተሩም የላቀ ድርሻን እየተወጣ እንደሚገኝ ገልጸዋ፡፡

አቶ ጃሚዕ አክለውም መምህራኑ ከስልጠናው የቀሰሙትን እውቀት ወደ ትምህርት ቤታቸው ሲመለሱ ለተማሪዎቻቸውና ለሌሎችም መምህራን  በማካፈል በትግበራው ላይም የጎላ አስተዋጾ እንደሚያበረክቱ ጠይቀዋል፡፡

ዘጋቢ ኢሊያስ መሀመድ 
28 5 13