ግንባታቸው ያልተጠናቀቁ ህንጻችን አገልግሎት የማስጀመር ክፍተት በሀረሪ ክልል ተንሰራፍቶ ይገኛል፡፡

ግንባታቸው ያልተጠናቀቁ ህንጻችን አገልግሎት የማስጀመር ክፍተት በሀረሪ ክልል ተንሰራፍቶ ይገኛል፡፡
ግንባታቸው ያልተጠናቀቁ ህንጻችን አገልግሎት የማስጀመር ክፍተት በሀረሪ ክልል ተንሰራፍቶ ይገኛል፡፡

ግንባታቸው ሳይጠናቀቁ አገልግሎት መጀመር የሚከለክል አዋጅ 624/2000 ን የሚተላለፍ ግለሰቦች ላይ ከ5 ዓመት እስራት እስከ 50 ሺ ብር ቅጣት እንደሚያስከትል አዋጁ ይደነግጋል፡፡

ነገር ግን ትላልቅ ህንጻች ከሆኑ እና ወጪያቸውም ትልቅ ከሆነ ደረጃ በደረጃ አገልግሎት መስጠት እንደሚችሉ ተቀምጧል፡፡

በሀረሪ ክልል የአዋጁ ተግባራዊነት በተመለከተ በክልሉ ከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ቢሮ የግንባታ ፍቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን ሀላፊ የሆኑት አቶ አብዱልአዚዝ አብዱራህማን ከሀረሪ ብዙሀን መገናኛ ኤጀንሲ ጋር ቆይታ አድርገው ነበር፡፡

እንደ ሀላፊው ገለፃ ከሆነ ግንባታቸው ሳያጠናቀቅ ይቅርና ግንባታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ እራሱ ጥራቱ ሳይረጋገጥ አገልግሎት መጀመር አዋጁ ይከለክላል ብለዋል፡፡

በሀረሪ ክልልም አዋጁ ተግባራዊነቱ አለመሆኑ እና የደረጃ በደረጃ ግንባታ የሚስፈልጋቸው ህንጻዎች የሉም ነው ያሉት፡፡

በተለይ ለኢንቨስትመንት ተብለው ተወስደው ታጥረው የተቀመጡ መሬቶችን እስከ መቀማት ደረጃ እርምጃ ወስደናል ብለዋል፡፡

ያላለቁ ህንጻች ላይ አገልግሎት መጀመር ከኢንቨስትመንት መቀዛቀዝ እስከ ከተማው ውበት መመበላሸት ተፅኖ እንዳለው ነው አቶ አብዱልአዚዝ የገለጹ፡

ላለፉት 2 እና 3 ዓመታት ችግሩ ጎልቶ እንደሚታይ የገለፁት አቶ አብዱልአዚዝ ይህ የሆነው በባለስልጣኑ ድክመት በመሆኑ ወደፊት የማሻሻያ ስራዎች ይሰራሉ ብለዋል፡፡

ባለሀብቶች ለአዋጁ ተግባራዊነት ቀዳሚው ድርሻ ስለሚወስዱ ለቀጣይ ስራቸው ያመች ዘንድ ህግን በማክበር እራሳቸውን ከተጠያቂነት እንዲጠብቁ አቶ አብዱላዚዝ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ዘጋቢ ነሲም መሀመድ ኑር 
25 5 13