እየተቀዛቀዘ የመጣውን የህረተሰቡን የንባብ ባህል ለማነቃቃት መንግስት የንባብ ማዕከላትን ማስፋፋት ላይ ትኩረት ሰቶ ሊሰራ ይገባል ሲሉ የከተማችን ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡

0
69

እየተቀዛቀዘ የመጣውን የህረተሰቡን የንባብ ባህል ለማነቃቃት መንግስት የንባብ ማዕከላትን ማስፋፋት ላይ ትኩረት ሰቶ ሊሰራ ይገባል ሲሉ የከተማችን ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡

ወጣቱም ቢሆን በየትኛውም አጋጣሚ እራሱን በንባብ በማበልጸግ ወደ ኋላ ማለት የለበትም ብለዋል፡፡

30.12.09

ማንበብ ነገሮችን በምክንያት እንድናከናውን ፈተናዎችን በብልሀት አንድናልፋቸው የሚያደርግ የህይወት ዘመን ስንቅ ነው፡፡

የማያነብ ማህበረሰብ በስሜት የሚመራና  ነገን አሳቦ  የማይንቀሳቀስ ይሆናል፡፡

በአለማችን በየግዜው ህወትን ቀላል ያደረጉ ፈጠራዎች ሁሉ የማንበብ ውጤቶች ናቸው፡፡

ታዲያ የሐረሪ ብዙሀን መገናኛ ኤጀንሲ በዛሬው እለት እተከበረ ያለውን የንባብ ቀንን ምክንያት በማድረግ በክልላችን ያለው የጥበብ ባህል ምን ይመስላል ሲል በሀረር ከተማ የሚገኙ ቤተመጽሀፍቶችንና ፤የመጽሀፍ መደብሮቹን ዳሷል፡፡

ጉዳዩን አስመልክቶ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች የከተማ ነዋሪ የንባብ ባህል ዝቅተኛ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡

በሐረር ከተማ በመጽፍ ሽያጭ ላይ የተሰማራው አቶ ዩናስ ለህረተሰቡ የንባብ ባህል መዳከም የወረቀትና የማተሚያ ዋጋ ከፍተኛ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ  የመጽሀፍ ዋጋ እየናረ  ከመምጣቱ ጋር የተያዘ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በርካታ ወጣቶች ከንባብ ይልቅ ሙዚቃ፤ማህበራዊ ድህረገጾችና ፊልሞች ያዘወትራሉ የሚሉት የወክማ ላይብረሪ ባለሙያ አቶ የሻነው በቀለ  የወጣቱን የንባብ ባህል ለማሳደግ ቤተ መጽሀፍቱ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ገልጻል፡፡

በቀጣይም ቤተመጽሀፍቱን በአዳዲስ መጽሀፍት ለማሰራጨት በዝግጅት ላይ መሆናቸውን  ነው የጠናገሩት፡፡

እነዚህ ያነጋገርናቸው የህረተሰብ ክፍሎች እየተቀዛቀዘ የመጣውን የንባብ ባህል ለመነቃቃት መንግስት የማንበቢያ ማዕከላትን ለማስፋት ላይ ትኩረት ሰቶ ሊሰራ ይገባል ብለዋል፡፡

ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል ያሉት እነዚህ አስተያየት ሰጪዎች ወጣቱ በየትኛውም አጋጣሚ ቢሆን እራሱን በንባብ ከማበልጸግ ወደ ኋላ ማለት የለበትም የሚል መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ዘጋቢ ትህትና ተስፋዬ

NO COMMENTS