6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ ፒሊስ ብሎም ቁመና ላይ ሊቀም እንደሚገባ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ገለፁ፡፡

6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ ፒሊስ ብሎም ቁመና ላይ ሊቀም እንደሚገባ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ገለፁ፡፡

ለክልሉ ፖሊስ አባላት ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቋል፡፡

 

የሐረሪ ክልል መንግስት  6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰላምና ፀጥታው የተጠበቀ እንዲሆን የክልሉን የፖሊስ አባላት በሑርሶ ፖሊስ ማሰልጠኛ ተቋም ለ15 ቀናት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቆ በዛሬው እለትም አስመርቋል።

 

የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድሩ አክለውም  አቶ ኦርዲን በድሪ እንደገለፁት ፖሊስ ዘመን ተሻጋሪ የሰላም ዘብ ጠባቂ  መሆኑን ገልፀው ከፍተኛ  የአገሪቱ ሐላፊነት ያለበት ትልቅ የሕግ አካል  ነው ሲሉ ጠቁመዋል።

 

ርዕሰ መስተዳድሩ   አክለውም በአገሪቷ ለ6ኛ ግዜ የሚካሔደው ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ ፖሊስ በብቁ ቁመና ላይ መገኘት  ሞያዊ ግዴታው መሆኑን አውቆ ጠንክሮ መሥራት እንደሚጠበቅበትም አሳስበዋል ።

 

የሐረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ናስሪ ዘከሪያ በበኩላቸው ከታሰበው ከ860 ፖሊስ አባላት  625 አባለት  ለ15 ቀናት ሲሰጡ በነበሩት ስልጠናዎች የተካፈሉ መሆናቸውን ገልፀዋል ።

 

ኮሚሽነሩ አክለውም የወሰዱትን ስልጠና  በተግባር በማዋል በአግባቡ ሕግ የመስከበር ሥራን ሊያከናውኑ ይገባል ብለዋል  ።

 

የሐረሪ ክልል የሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ቢሮ ሐላፊ አቶ ናስር ዩያ በበኩላቸው እንደገለጹት ከፊታችን ግንቦት ወር የሚካሄደው ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ  ሁሉም አባላት ከፍተኛ ሀላፊነት እንዳለባቸው አስረድተዋል ።

 

ሐላፊው በማያያዝም የክልሉን ሰላም በመጠበቅ ሰላምን የሚያናጉ ማንኛውም አካሄደን አስቀድሞ ማክሰም እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

 

በስልጠናው በስራ አፈፃፀማቸው ከፍተኛ ውጤት የስመዘገቡ የፖሊስ አባላትና አመራሮች የማዕረግና የዋንጫ ሽልማቶች በክልሉ ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ኦርዲን በድሪ እጅ የተቀበሉ ሲሆን ለሑርሶ ፖሊስ ማሰልጠኛ ተቋምና ለምሥራቅ ዕዝም የዋንጫ ሽልማት ተበርክቶለታል ።

 

ኢሊያስ መሀመድ

2 8 13