በሀገር አቀፍ ደረጃ ለወጣቱ የስራ እድል ፈጠራ የተመደበው በጀት የወጣቱን ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን ያረጋገጡ መሆኑን የሐረሪ ክልል የሴቶች ህጻናትነማ ወጣቶች ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡

0
86

በሀገር አቀፍ ደረጃ ለወጣቱ የስራ እድል ፈጠራ የተመደበው በጀት የወጣቱን ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን ያረጋገጡ መሆኑን የሐረሪ ክልል የሴቶች ህጻናትነማ ወጣቶች ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡

   በዘንድሮ አመት በክልሉ የተለቀቀው 13 ሚሊን ብር ላይ በማህበር የተደራጁ ወጣቴች እስከ 5 ሚሊየን ብር ወጪ እንደሆነ የጽ/ቤቱ ሀላፊ ወ/ሮ ሀናን ዱሪ ገልጸዋል፡፡

29.12.09

የሐረሪ ክልል የሴቶች ህጻትና ወጣቶች ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ሀናን ዱሪ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደተናገሩት በክልሉ በስራ አጥነት ከተመለመሉት 4000 ወታቶች ስልጠና ወስደው ያጠናቀቁ 2100 ወጣቶች መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

ከነዚህ 2100 ከሆኑት ወጣቶች 81 ማህራት በንግድ 40 የሚሆኑት በሙያ 102 የሚሆኑት በገጠር ምግብ ዋስትና ተደራጅተው ወደ ስራ መግባታቸውን ነው ወ/ሮ ሀናን የገለጹት፡፡

እነዚህ የተደራጁ ወጣቶችን ወደ ስራ ለማስገባት እስከ 5 ሚሊየን  ብር የመስሪ ዕቃ ግዢ እንደተላለፍላቸው አብርተዋል፡፡

ለወጣቱ የስራ እድል ፈጠራ የተመደበው በጀት የወጣቱን ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን ያረጋገጡ መሆኑንም ነው የገለጹት፡፡

ለወጣቱ ስራ እድል ፈጠራ የተመደበው በጀት የህዝብ ሀብት መሆኑን የጠቆሙት ሀላፊዋ በዚህ ሂደት ውስጥ ያለአግባብ በተለይም በቤተሰብ ስም የተደራጁ እና ኢንቨስተር የተገኘባቸው 19 ማህበራት እንዲፈርሱ መደረጉንም ገልጸዋል፡፡

ዘጋቢ ኢሊያስ ኢብራሂም

NO COMMENTS