በሐረሪ ክልል በስራ እድል ፈጠራ ዙሪያ እየተሰራ ያለው ስራ የወጣቱን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ያረጋገጠ መሆኑን የሰቶች ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ጽ/ቤቱ ሀላፊ ወ/ሮ ሀናን ዱሪ ተናገሩ፡፡

0
107

በሐረሪ ክልል በስራ እድል ፈጠራ ዙሪያ እየተሰራ ያለው ስራ የወጣቱን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ያረጋገጠ መሆኑን የሰቶች ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ጽ/ቤቱ ሀላፊ ወ/ሮ ሀናን ዱሪ ተናገሩ፡፡

በወጣቱ የስራ እድል ተጠቃሚነት ዙሪያ በማህበራዊ ድህረ ገጾች የተሳሳተ መረጃ የሚያሰራጩ ግለሰቦች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የጽ/ቤት ሀላፊ አስታውቀዋል፡፡

1.13.09

መንግስት የክልሉን ወጣቶች የስራ እድል ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ 27 ሚሊየን ብር መድቦ ሲንቀሳቀስ ቆይቷል፡፡

በዚህ ሂደትም 4 ሺ የሚሆኑ ስራ አጥ ወጣቶች በህብረተሰቡ ቀጥተኛ ተሳትፎ ተመልምለው በስራ ዕድል ፈጠራው እንዲካተቱ ተደርጓል፡፡

እስከ አሁን ባለው መረጃም በፕሮግራሙ አማካኝነት በርካታ ወጣቶች ስልጠና  አጠናቀው ወደ ስራ መግባት መጀመራቸውን የክልሉ ሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ሀናን ዱሪ ገልጸዋል፡፡

የወጣቶች የስራ እድል ፈጠራው ፕሮግራም ገና ከመነሻው ከምልመላው አንስቶ ፍትሀዊ ለማድረግ ከፍተኛ ስራ መሰራቱንም ሀላፊዋ የገለጹት፡፡

በስራ እድል ፈጠራው በቤተሰቡ ስም፤ የተደራጁና ባለሀብቶች የተካተቱባቸው 19 ማህበራት በጽ/ቤቱ አማካኝኘት እንዲፈርሱ መደረጉን ለአብነት በማንሳት፡፡

ሆኖም በአንዳንድ አካላት የስራ እድል ፈጠራው ፍትሀዊ አይደለም የሚል የተሳሳቱ መረጃ በማህበራዊ ድህረ ገጾች አማካኝነት እየተሰራጨ መሆኑ ተናግረዋል፡፡

ይህ ከሰሞኑን  በማህበራዊ ድህረ ገጽ እየተሰራጨ ያለ  አሉባልታ ፍጹም   ከእውነት የራቁና ተጨባች ያልሆነ  መሆኑን   የጠቆሙት ወ/ሮ ሀናን  ህብረተሰቡ በዚህ  አይነት አሉባልታ መደናገር የለበትም  ብለዋል፡፡

በመጨረሻም በተለያዩ ማህራዊ ሚዲያዎች ህብረተሰቡን የተሳሳተ አመለካከት  ለማስያዝ ተብሎ የተሳሳተ መረጃዎችን የሚያሰራጩ ግለሰቦች ከዚህ አፍራሽ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡም አሳስበዋል ፡፡

NO COMMENTS