የሐ/ክ ሴቶች ህጻናት እና ወጣቶች ጉዳይ ጽ/ቤትበክልሉ የሚገኙ የተለያዩ ሴክተር ቢሮዎች በመዘዋወር መጪው አዲስ አመት የፍቅር፤የሰላም የስራና የብልጽግና እንዲሆን ያለውን መልካም ምኞት ገለጸ፡፡

0
92

የሐ/ክ ሴቶች ህጻናት እና ወጣቶች ጉዳይ  ጽ/ቤት በኩል የተዘጋጀ ልኡካን ቡድን በትላንትናው እለት መነሻውን የክልሉ ፕሬዘዳንት ጽ/ቤት በማድረግ በክልሉ የሚገኙ የተለያዩ ሴክተር ቢሮዎች በመዘዋወር መጪው አዲስ አመት የፍቅር፤የሰላም የስራና የብልጽግና እንዲሆን ያለውን መልካም ምኞት ገልጸዋል፡፡

በዚህም ወቅት የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጉብንት ለመጪው አዲስ አመት የስራ መነቃቃትን እንደሚፈጥርላቸው በመግለጽ ለመላው የኢትጵያ ህዝብ እንኳን ለ2010 ዓ.ም ዘመን መለወጫ በዓል አደረሳችሁ ብለዋል፡፡

3.13.09

የ2010 ዓ.ም ዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ በሀረሪ ክልል ሴቶች ህጻናት እና ወጣቶች ጉዳ ጽ/ቤት የተመራ የልኡካን ቡድን ለክልሉ ለርእሰ መስተዳድር አቶ ሙራድ አብዱልሃዲ  እንኳን ለ2010 ዓ.ም ዘመን መለወጫ በዓል በሰላም አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኖታቸውን ገልጸዋል፡፡

የልኡካን ቡድኑ በ2010 የስራ ዘመን  የሴቶችና የወጣቶችን  ተጠቃሚነትን ለማረጋጥ በሴቶች እና ህጻናት ላይ የሚደርሱ  ጥቃቶችንና ትንኮሳዎችን ለማስቆም  የክልል ሴክተሮች የሴቶችን ፤የህጻናትን እና የወጣቶችን የስርኣተ ጾታ እኩልነት አንዲያካትቱ  ለማድረግ እንደሚሰራ አስታውቋል፡፡

እነዚህን ስራዎች  ውጤታማ ለማድረግ  ርእሰ መስተዳድሩ ከጎናቸው እንዲቆሙ በሐረሪ ክልል ሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ጽ/ቤት ስም የልኡካን ቡድኑ ጠይቀዋል፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙራድ አብዱልሀዲ በእዚሁ ግዜ እንዳሉት  የሐረሪ ሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ጽ/ቤት የባለፉት አመታት የስራ እንቅስቃሴ የሚበረታታ መሆኑን ገልጸው መጪው አዲስ አመት የስራ ዘመንም  የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ መስራት እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡

የክልሉ መንግስትም  ድጋፍ ከጽ/ቤቱ እንደማይለያም ርእሰ መስተዳድሩ አረጋግጠዋል፡፡

ከዚህም በመቀጠል የልኡካን ብድኑ በከልልሉ በሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች  በመዘዋወር በ2010 ዓ.ም የስራ ዘመን የሀረሪ ሴቶች ህጻናት እና ወጣቶች ጽ/ቤት በሚደርገው የስራ እንቅስቃሴ ውስጥ በንቃት እንዲሳተፉ  ጠይቀዋል፡፡

አዲሲ ዓመት የፍቅር፤የሰላም ፤ እና የብልጽግና እንዲሆን የልኡካና ቡድኑ በሐረሪ ሴቶች ህጻናትናወጣቶች ጉዳይ  ጽ/ቤት ስም መልዕክት አስተላልፏል፡፡

ዘጋቢ አሊያስ አርጋው

NO COMMENTS