በህንድ ፋሩቅሀባድ በተባለ ስፋራ በርካታ ጨቅላ ህጻናት መሞታቸው በሀገሪቱ አነጋጋሪ እና አሳዛዥ ክስተት እየፈጠረ ይገኛል፡፡

0
54

በህንድ ፋሩቅሀባድ በተባለ ስፋራ በርካታ ጨቅላ ህጻናት መሞታቸው በሀገሪቱ አነጋጋሪ እና አሳዛዥ ክስተት እየፈጠረ ይገኛል፡፡

በሆስፒታሉ አንድ ወር በሚሆን ግዜ 49 የሚሆኑ ህጻናት የሞቱ ሲሆን አብዛኞቹ ህጻናትም በኦክሲጅን እጥረት አማካኝነት ሂወታቸውን ማጣታቸው ተናግሯል፡፡

 30.12.09

ፋሩቅሀባድ ተብሎ በሚጠራው የህንድ ስፍራ የሚገኘው ሆስፒታል በርካታ ህጻናት በአንድ ወር ግዜ መሞታቸው አስደንጋጭ ክስተት ፈጥሯል፡፡

የ49 ህጻናት ሞት መንስኤ በሆነው ጉዳይ የሀገሪቱ ፖሊስ ተገቢ የሆነ ምርምራ እያካሄደ መሆኑን ሲገልጽ 30 የሆኑት ህጻናት ከኦክሲጂን እጥረት ጋር በተያያዘ ችግር ሂወታቸውን ሊጡ መቻላቸውን ተነግጓል፡፡

ራም ማያሀር ሌሐያ ሆስቲፓል በአንድ ወር ግዜ 49 ህጻናት ሲሞቱ በዚህቹ የህንድ ግዛት 160 ህጻናት በተመሳሳይ ችግር ሒወታቸውን ያጡ መሆናቸውም ጉዳዩን አሳሳቢ እንዲሆን አድርጎታል፡፡

በቅርቡ በተካሄደው ምርመራ መሰረት የሀገሪቱ መንግስት የሆስፒታል አባላቶችን ለችግሩ ተወቃሽ አድርጓል፡፡

በጉዳዩ ሌላ  ምርመራ እንደሚያስፈልግም  እየተነገረ ነው ፡፡

የሐገሪቱ ፖሊስ በሰጠው መግለጫ መሰረት ሆስፒታሉ ህጻናቱ በሚወለዱበት ወቅት ኢክሲጅን እንዲገኙ ትቦ አልተተከለላቸውም ነበር ተብሏል፡፡

ይህች የህንድ ክልል የሆነችው ፋሩቅሀላድ ግዛት በህንድ ከሚገኙ ክልሎች በገቢ መጠኗ አንስተኛ እና ድህነት የሚስተዋልባት ናት፡፡

ህጻናት በተለያዩ ህመመሞች በግዛቷ በሰፊው ሂወታቸውን እንደሚያጡበት መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

የቢቢሲ ገዘባን በሀር ጠንክር አዘጋጅቶታል፡፡

NO COMMENTS