የኢድ አል አድሀ በዓልን ስናከበር የተጀመረውን ልማት በማስቀጠል ሊሆን እንደሚገባ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሙራድ አብዱልሀዲ ተናገሩ፡፡

0
79

 

የኢድ አል አድሀ በዓልን ስናከበር የተጀመረውን ልማት በማስቀጠል ሊሆን እንደሚገባ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሙራድ አብዱልሀዲ ተናገሩ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ ይህን የገለጹ የ1438ተኛው የአረፋ በዓልን አስመልክቶ ለሀረሪ ብዙሀን መገናኛ ኤጀንሲ በሰጡት አስተያየት ነው፡፡

26.12.09

በመላው አለም የሚገኙ የእስልምና  እምነት ተከታዮች ዘንድ 1438ተኛው የአረፋ በዓል በደማቅ ስነ ስርዓት እየተከበረ ይገኛል፡፡

በሀረሪ ክልል በኢማም አህምድ ስታዲየምም በዓሉ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ የእስልምና እምነት ተከታዮች በተገኙበት ተከብሯል፡፡

የኢድ አል አድሀ በዓልን አስመልክቶ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙራድ አብዱልሀዲ ለሐረሪ ብዙሀን መገናኛ ኤጀንሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት የአረፋ በዓል ስናከበር የጀመርነውን ልማት በማስቀጠል ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡

የበዓሉ ታዳሚዎች በበኩላቸው የአረፋ በዓል አንድነታችንን የምናጠናክርበትና ለቀጣዩ ትውልድ አብሮነታችንን  የምናስተላልፍበት ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በዓሉ የአንድነት እሴታችንን የምናጠናክርበት ነው ያሉት ታዳሚዎቹ በዓሉ አገራችንን የምንገነባበት ሊሆን ይገባልም ብለዋል፡፡

1438ተኛው የኢድ አል አድሀ  በዓል በመላው አለም በሚገኙ  ከ 1.8 ቢሊዮን በላይ በሚሆኑ የእስልምና  እምነት ተከታዮች ዘንድ በደመቀ ሁኔታ እየተከበረ ይገኛል

ዘጋቢ አሚር ኡስማን

NO COMMENTS