የሐረሪ ክልላዊ መንግስት አዲስ አመትን አስመልክቶ ለ18 ታራሚዎች ምህረት አደረገ፡፡

0
74

የሐረሪ ክልላዊ መንግስት አዲስ አመትን አስመልክቶ ለ18 ታራሚዎች ምህረት አደረገ፡፡

እነዚህ ምህረት የተደረገላቸው ታራሚዎች ህረተሰቡን ሲቀላቀሉ የበደሉትን ህዝብ መካስ እንዳለባቸው ተገልጻል፡፡

3.13.09

የሐረሪ ክልላዊ መንግስት አዲስ አመትን አስመልክቶ ለታራሚዎች ይቅርታና ምህረት ማድረጉን የሐረሪ ክልል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ሬድዋን አዱሱ ገልጸዋል፡፡

አዲስ አመትን አስመልክቶ ይቅርታ ከተደረገላቸው 18 ታራሚዎች ውስጥ 14ቱ ሙሉ በሙሉ ከእስር የሚፈቱ ሲሆን 4 ቱ ደግሞ ከእድሜ ልክ እስራት ወደ 23 አመት ጽኑ እስራት የተቀየረላቸው መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ለታራሚዎቹ የተደረገው ይቅርታ ከመስከረም 1 2010 ዓ.ም ጀምሮ ተግባር ላይ እንደሚውልም ነው የተናገሩት፡፡

እነዚህ ምህረት የተደረገላቸው ታራሚዎች ህብረተሰቡን ሲቀላቀሉ የበደሉትን ህዝብ መካስና አምራች ዜጋ መሆን እንዳለባቸውም  አቶ ሬድዋን ገልጸዋል፡፡

ኮሚሽነሩ ለመላው የክልሉ ነዋሪ እንኳን ለ2010 ዓ.ም በሰላም አደረሳችሁ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

አዲሱ አመትም የሰላምና የብልጽግና እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

ዘጋቢ ሰይፉ ጌታቸው

NO COMMENTS