ባለፉት አስርት አመታት በትምህርት፤በንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትና በመሰረተ ልማት የተከናወኑ ስራዎች የክልሉን ህዝብ በተለይም የገጠሩን ህብረተሰብ ተጠቃሚነት ያረጋገጡ መሆናቸውን የሐረሪ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሙራድ አብዱልሃዲ ተናገሩ፡፡

0
79

ባለፉት አስርት አመታት በትምህርት፤በንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትና በመሰረተ ልማት  የተከናወኑ ስራዎች የክልሉን ህዝብ በተለይም የገጠሩን ህብረተሰብ ተጠቃሚነት ያረጋገጡ መሆናቸውን የሐረሪ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሙራድ አብዱልሃዲ ተናገሩ፡፡

የወጣቱን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ፤ መልካም አስተዳደርን ማስፈንና ኪራይ  ሰብሳቢነትን መዋጋት የቀጣይ አመታት የክልሉ መንግስት የትኩረት አቅጣጫዎች መሆናቸውን ርእሰ መስተዳድሩ ገልጻል፡፡

3/13.09

ርእሰ መስተዳድሩ ባለፉት አስርት አመታት በመሰረተ ልማት ዝርጋታ፤በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፍ ክልሉ ረዥም ርቀት መጓዝ መቻሉን በመግለጫቸው ጠቁመዋል፡፡

በእነዚህ አመታት በተለይም በክልሉ የትምህርት ሽፋንን ከማሳደግ አኳያ አበረታች ሊባል የሚችል ስኬት መመዝገቡን ነው የተናገሩት፡፡

የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ብዛት 120፤የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን 8፤ የቴክኒክ ሙያ ትምህርት መስጫ ማእከላት ቁጥር 6 መድረሳቸው በዘርፉ ለተመዘገበው ስኬት ለአብነት መቅረብ የሚችሉ ማሳያዎች መሆናቸውን በመጠቆም፡፡

ያለፉት አስርት አመታት የክልሉ ገጠር አካባቢ ህዝቦችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በመንግስት በኩል በስፋት  መሰራቱን የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ በተለይ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ሽፋንን ከማሳደግና የኤሌክትሪክ ሀይል ተጠቃሚነትን ከማረጋገጥ አንጻር የተከናወኑ ስራዎች አበረታች ናቸው ብለዋል፡፡

ወረዳን ከወረዳ በመንገድ ከማገናኘት አኳያ ያለፉት አስርት አመታት የክልሉ መንግስት ውጤታማ ስራ ያከናወነበት  ጭምር መሆኑን ርእሰ መስተዳድሩ በመግለጫቸው ተናግረዋል፡፡

በክልሉ በሁሉም ዘርፍ የተከናወኑት  የልማት ስራዎች የክልሉ ህዝብ ተሳታፊነቱና ተጠቃሚነቱ የተረጋገጠበት ነው ብለዋል፡፡

በዋነኛኘትም በክልሉ አዘጋጅነት የተከበሩት 11ኛው የብሄሮች ፤ብሄረሰቦች ህዝቦች ቀንና 22ተኛው አለም አቀፍ የሐረር ቀን አስመልቶ የተከናወነ የመሰረተ ልማት  ግንባታዎች ነዋሪው በዘላቂነት ተጠቃሚ ያደረጉ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

የክልሉ መንግስት በአስር አመታት ጉዞው ከኪራይ ሰብሳቢነት፤ከመልካም አስተዳደርና ከጥበት ጋር ተያይዞ ያጋጠሙትን እንቅፋቶችንም ህዝቡን ከጎኑ አሰልፎ ባደረገው ትግል ድል መንሳት መቻሉንም ጠቁመዋል፡፡

የወጣቱን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ፤መልካም አስተዳደርን ማስፈንና ኪራ ሰብሳቢነትን መዋጋት የቀጣይ አመታት የክልሉ መንግስት የትኩረት አቅጣጫ መሆናቸውን ርዕሰ መስተዳድሩ በመግለጫቸው አስታውቀዋል፡፡

ዘጋቢ ቶሎሳ በየነ

NO COMMENTS