በትራንስፖርት እጥረት እየተቸገሩ መሆናቸውን የሐረር ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡

0
71

በትራንስፖርት እጥረት እየተቸገሩ መሆናቸውን የሐረር ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡

የመንገድና ትራንስፖርት ጽ/ቤት በክልሉ ችግሩን ለመቅረፍ የተለያዩ አማራቾችን እየተጠቀምኩ ነው ብሏል፡፡

30.12.09

የክልሉ መንግስት በከተማ የሚስተዋለው የትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍ የተለያዩ አማራጮችን ሲጠቀም ቆይቷል፡፡

በቅርብ ግዜ እንኳ ችግሩን ይቀርፋል በሚል በትራንስፖርት መጓጓዣ ታሪፍ ላይ ማሻሻያ መደረጉን ይታወሳል፡፡

ሆኖም ይህ ሁሉ የመንግስት ጥረት ሊያቃልለው አለመቻሉን የሐረሪ ክልል ብዙሀን መገናኛ ኤጀንሲ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡

በተለይም አሁንም ቢሆን የቲቪኤስ ባጃጆች ከኮንትራት ውጪ በመደበኛ ዋጋ የትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጡን አይደለም ብለዋል፡፡

በትራንስፖርት ችግር የተነሳ ለተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫናዎች እየተጋለጠ ነው ያሉት ነዋሪዎቹ መንግስት ችግራቸውን በዘላቂነት እንዲፈታላቸው ጠይቀዋል፡፡

የነዋሪዎቹ ቅሬታ አስመልክቶ ያነጋገርናቸው የትራንስፖርት ጽ/ቤት የትራፊክ ቁጥጥር ዋነ ስራ ሂደት ባለቤት አቶ ሳላህ አቡበከር ጽ/ቤቱ የተለያዩ አማራጮችን ተጠቅሞ ችግሩን ለመፍታት ጥረት እያደረገ ነው ብለዋል፡፡

ችግሩን በዘላቂነነት ለመቅረፍ የህረተሰቡ ተሳትፎ መሆኑን የገለለጹት አቶ ሳላህ የትራንስፖርት ተገልጋዩ ከኮንትራት ውጪ አንንቀሳቀስም የሚሉ አሽከርካሪዎች ሲያጋጥመው ለሚመለከተው አካል እንዲጠቁም ጠይቀዋል፡፡

ዘጋቢ ሳዩ አብዱራህማን

 

 

NO COMMENTS